ገንዘብ ሲናገር ፍትሕ ዝም ይላል!
ሦስት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጆች ከ6ሺ በላይ ተማሪዎችን አስመረቁ
በትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ሙሉ ዕውቅናን አግኝተው ማስተማር ከጀመሩት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጆች መካከል ሦስቱ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጆች ከ6 ሺ በላይ ተማሪዎችን አስመረቁ፡፡
ጉራጌን በ"ዮኸምያ ክትፍወ በጉየ ተኸራር"
በሔኖክ ያሬድ
"ኢትዮጵያ ሀገሬ መመኪያዬ ክብሬ" የሚለው ዘፈን እያቀነቀንኩ ነበር፡፡ ነሐሴ 25 ቀን 2000 ከዮኸምያ በጉየ ተኸራር የጉራጌ የባህል ማዕከል የወጣሁት፡፡ ዘፈኑ እንዴት እንደመጣልኝ ይገርመኛል፡፡ ሞዛይክ ከምትባለዋ ሁሉንም አሰባስባ ከያዘችው ኢትዮጵያ አንዱ ገጽታ ጉራጌ ውስጥ ገባሁ፡፡
ሽቶ ላልተወለዱ ልጆች አደገኛ ነው
የሥነ ተዋልዶ ጤና በከፍተኛ...
የዋና አዘጋጁ እስር ሌሎችንም ይነካካል
ሃብታሙ በቀለ
ያለፈው ሳምንት ሃገረኛዎቹና የውጭ ሚዲያ ጭምር ሰፊ ሽፋን የሰጡት የሪፖርተር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ፣ ከሕግ ውጭ በሆነ አያያዝ ተገዶ ወደ አማራ ክልል ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ፣ የመታሰሩን ዜና ነበር፡፡ በሪፖርተር ጋዜጣና በሌሎች የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪዎች ድረ ገፅ ላይ በስፋት የተተነተነበት የክልሉ ፖሊስና ፍርድ ቤት "አያገባቸው ገብተው አያወዛቸው ተቀብተው" ያለ ሥልጠናቸውና ያለመብታቸው መብት መድፈር ሕገ ወጥነት መሆኑም ሲጠቀስ ሰንብቷል፡፡
ከሁለት ሴት ልጆቻቸው ጋር በመሆን የተለያዩ ሥልጠናዎችን የሚያዘጋጅና ጥናቶችን የሚያደርግ ኤንታክ (NTAC) ኢንተርናሽናል የተባለ ድርጅት አቋቁመዋል፡፡ ሁለተኛ ልጃቸው የድርጅቱ ዳይሬክተር፣ እሳቸው ደግሞ ምክትል፣ የመጀመሪያ ልጃቸው ደግሞ የውጭ ግንኙነት ሆና በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡
"ዓባይ መነኰሰ"፣ "ተከዜ አረጀ አሉ" እንጉርጉሮ እንዲቀር"
በፍሥሐ ገብረ ኪዳን
የዓባይ ድልድይ በያዝነው የ2000 ዓመት መሰናበቻ ጳጉሜ ወር መጨረሻ ላይ እንደሚመረቅና "ሕዳሴ" የሚል ስም እንደሚሰጠው፣ በምረቃውም ዕለት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እንደሚገኙ የዘገበው የሪፖርተር ጋዜጣ የነሐሴ 25 ቀን ዜና ማንበቤን ተከትሎ ነው በዚህ ጉዳይ ላይ አንዳንድ ጉዳዮችን ለምን አላነሳም ብዬ የወሰንኩት፡፡ በጃፓናውያን ድጋፍና ወጪ የተሰራው ድልድይና መንገድ የሚመረቀው ገና ጳጉሜ 5 ቀን ቢሆንም ሕዳሴ የሚል ስያሜ እንደሚሰጠው የመገለጹ ወሬ እውነት ከሆነ በምረቃው ሥነሥርዓት ላይ የሚገኙትን ባለሥልጣናት ከፍተኛነትና ምናልባትም ማንነት እሱ ራሱ ብቻውን ያመለክታል ብዬ እጠረጥራለሁ፡፡
የአካል ጉዳተኞች የሥራ ስምሪት መብት አዋጅ
በሰለሞን ጎሹ
በ1986 ዓ.ም. የወጣው የአካል ጉዳተኞች የሥራ ሥምሪት መብት አዋጅ ቁጥር 101/1986 ከ14 ዓመታት ቆይታ በኋላ እየተገባደደ ባለውና በያዝነው ዓመት መጋቢት ወር በ"የአካል ጉዳተኞች የሥራ ሥምሪት መብት አዋጅ ቁጥር 568/2000" ተሽሯል፡፡
የማታ ማታ ብዙ ሰዎች ለርጅና እጅ ሳይሰጡ ለአገራቸው እንዲሁም ለሌላውም ህዝብ አያሌ ጠቃሚ ነገር አበርክተው እንዳለፉ ትሪካቸው ያስረዳል፡፡ ለምሳሌ ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉት ሰዎች በአራያነታቸው ይጠቀሳሉ፡፡
በምሕረት አስቻለው
ከአምስት ወራት በፊት የኩላሊትና የሳንባ ህመም እንዳለባቸው ተነግሯቸው የተለያዩ ሕክምናዎችን አድርገዋል፡፡ ነገር ግን ከሕክምና በኋላም ፈውስ ማግኘት አልቻሉም፡፡ አንድ ቀን ዘወትር ወደ ሆስፒታል ያመላልሳቸው የነበረው የመጀመሪያ ልጃቸው "እማዬ የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደምሽ ውስጥ ቢኖር ምን ታደርጊያለሽ?" የሚል ድንገተኛ ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡ ቫይረሱ በደማቸው ይገኛል የሚል ጥርጣሬ ፈፅሞ እንደሌላቸው፣ ቢኖርባቸውም መኖር እንደሚችሉ ለልጃቸው ይነግሩታል፡፡
"መንግሥት ጥፋተኛው ማን እንደሆነ አጣርቶ ውሳኔ ይስጥ"
ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ባለፈው ሠኞና ማክሰኞ 26 እና 27 ቀን 2000 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ በጉባኤው ከቀረቡት አጀንዳዎች መካከል አንዱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ፣ ከፊፋ እና ካፍ ጋር ስለነበረው ሁኔታ የሚመለከት ሲሆን፣ ጉባኤው ባለው ማንዴት መሰረት የቀረቡትን ሪፖርት በመመርመር ውሳኔ አሳልፏል፡፡
የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ ምክትል ኘሬዚዳንቷ የቤተሰብ ጉዳይ ውዝግብ ፈጥሯል
በኃይሌ ሙሉ
ለአቅመ ሄዋን ሳይደርሱ የሚከሰት እርግዝና አሜሪካ ውስጥ የፖለቲካ ጉዳይ በሆነበትና የልጅ እናቶች ሥራ እንዲሰሩ መገደዳቸው የሞራል ክርክር እያስነሳ ባለበት በአሁኑ ወቅት የሪፐብሊካኑ እጩ ኘሬዚዳንት ጆን ማኬይን የአላሳካ ገዢ የሆኑትን ወ/ሮ ሳራ ፔሊን ምክትል ኘሬዚዳንት አድርገው መምረጣቸው ትልቅ ውዝግብ ፈጥሯል፡፡
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |
Share your thought and ideas with others on our public forum. Just register here and participate on our new and improved forum. Note that all members of the old version forum have to register again to post on the new version forum.