የግብፅ ፕሬዚዳንት በኬንያ ባደረጉት ይፋዊ ጉብኝት አገራቸው በዓባይ ወንዝ ጉዳይ ከተፋሰሱ አገሮች ጋር ለመተባበር፣ ከአባልነት ራሷን ካገለለችበት የናይል ቤዚን ኢንሼቲቭ ጋር ደግሞ በድጋሚ ለመነጋገር የሚያስችል የተለሳለሰ አቋም አሳዩ፡፡

ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ ሰባተኛውን የከተሞች መድረክ (ፎረም) ለማስተናገድ እየተዘጋጀች ነው፡፡ ከሚያዝያ 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በሚቆየው መድረክ 200 ከተሞች፣ የእነዚህ ከተሞች እህት የሆኑ የውጭ አገር ከተሞችና 20 ኩባንያዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

ከሁለት ማከፋፈያዎች የኤሌክትሪክ ኃይል የምታገኘው የበርካታ ኢንዱስትሪዎች መናኸሪያ ሞጆ ከተማ አንደኛው ማከፋፈያ በገጠመው ብልሽት ምክንያት ከየካቲት 11 እስከ 13 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ በከፊል ጨለማ ውስጥ የቆየች ቢሆንም፣ መስመሩ ተስተካክሎ ሙሉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘቷ ተገለጸ፡፡

Pages