አቶ ተስፋዬ መንግሥቴ፣ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ዴኤታ

የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር የመኸር እርሻ እንቅስቃሴ፣ የግብዓት አቅርቦትና አጠቃቀም ያለበትን ደረጃ እንዲሁም በቀጣይ በትኩረት መሠራት ስለሚያስፈልጋቸው ጉዳዮችና በበልግና በመኸር ሰብሎች ላይ ጥቃት በማድረስ ላይ የሚገኘውን የአሜሪካ ተምች አስመልክቶ ሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ.ም. መግለጫ ሰጥቶ ነበር፡፡

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል በመካሄድ ላይ ያለውን አገር አቀፍ ጥረት በበላይነት የሚያስተባብር፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሚመራና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትን የሚያቅፍ ብሔራዊ ምክር ቤት እንዲቋቋም ተጠየቀ፡፡

«ሽብርተኝነትን ከሚዋጉት የአፍሪካ አገሮች ጋር ትብብራችንን እናረጋግጣለን።  የሽብርተኝነት ሥጋት የተፈጠረው የአካባቢው አገሮች ባልሆኑ፣ በተለይም ምዕራባውያን አገሮች በአካባቢው የማይመቿቸውን መንግሥታት ዓለም አቀፍ ሕግን በመጣስ ለማውረድ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ይዘው በተንቀሳቀሱበት ጊዜ ነው።»

ሐቻምና በምሥራቅ አዲስ አበባ ኢምፔሪያል አካባቢ ተተክሎ የነበረው የቦብ ማርሌ ሐውልት፣ በመስቀለኛ መንገድ የማስፋፋት ሥራ ሳቢያ ሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ.ም. እንዲነሳ ተደርጓል፡፡

በኢትዮጵያ የጽሕፈት/የሥነ ጽሑፍ ታሪክ ከሦስት ሺሕ ዓመታት በላይ እንዳስቆጠረ ይነገራል፡፡ በተለይ በዘመነ አክሱም ከመጀመሪያው ምዕት ዓመት ወዲህ የጽሕፈት ባህሉ ከድንጋይ ላይ ተጀምሮ ወደ ብራና መሸጋገሩ በርካታ የጽሑፍ ቅርሶች መያዙም ይታወቃል፡፡ 

Pages