ካለፉት አራት ወራት ወዲህ በበቆሎ ላይ የታየው የአሜሪካ መጤ ተምች በአገሪቱ መጀመርያ ከታየበት ከደቡብ ጀምሮ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላና ትግራይ ክልሎች በ135 ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ የተዘራ በቆሎ ማጥቃቱ ተገለጸ፡፡ በክልሎቹ ከተዘራው አንድ ሚሊዮን ሔክታር በቆሎ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የወደመ እንደሌለም ተጠቁሟል፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ጃክሮስ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ የረር ጎሮ በሚወስደው መንገድ፣ ሰኔ 9 ቀን 2009 ዓ.ም. ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ የራሱን ሚኒባስ እያሽከረከረ ወደ ቤቱ በመጓዝ ላይ የነበረ የ26 ዓመት ወጣት በመደብደብ ሕይወቱ እንዲያልፍ አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ ከአምስት በላይ ፖሊሶች መታሰራቸው ተጠቆመ፡፡ 

Pages