‹‹የታታሪዎች ዕንቁ የሆኑትን እኚህን አገር ወዳድና የአገር አገልጋይ ሃይማኖተኛ ሰው፣ [ሀብተ ሥላሴ ታፈሰ] በዚህ በተቀደሰ ቦታ ተገኝተን ለመጨረሻ ጊዜ ስንሰናበታቸው መልካም ሥራቸውና ሰብዕናቸው እየታሰበን ነው፡፡››

‹‹እንደ ብዙዎቹ ታላላቅ የሥራ መስኮች ሁሉ አቶ ሀብተ ሥላሴን ከቱሪዝም ሙያ ጋር ያገናኛቸውና ከዚህ ዓለም በሞት እስከተለዩበት ቀን ድረስ ከመስኩ ጋር ያቆራኛቸው አንድ አጋጣሚ የሚያስገርም ነበር፡፡ 

የቱሪዝምን ጽንሰ ሐሳብ ኢትዮጵያ ውስጥ በማስተዋወቅ፣ የኢትዮጵያ ቱሪስት ድርጅት በመመሥረትና በዋና ሥራ አስኪያጅነት ያገለገሉት የአቶ ሀብተ ሥላሴ ታፈሰ ሥርዓተ ቀብር፣ እሑድ ነሐሴ 7 ቀን 2009 ዓ.ም. በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከረፋዱ 5 ሰዓት ይፈጸማል፡፡

Pages