የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር የእርሻ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ መንግሥቴ፣ በመኸር እርሻ እንቅስቃሴና በወቅታዊው የአሜሪካ ተምች ላይ ዓርብ ሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአገሪቱ ባለሙያዎች አዲስ የሆነው የአሜሪካ ተምች ለግብርናው ዘርፍ ከባድ ፈተና መሆኑንና በበቆሎ   ከተሸፈነው እርሻ በ135 ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ መታየቱን አስረድተዋል፡፡ 

ታላቋ ብሪታኒያ እ.ኤ.አ. ከ2000 በፊት ሽብርን አስተናግዳ ብታውቅም፣ ዘንድሮ እየገጠማት ያለውና በተለይ ከእስልምና አክራሪነትና እስልምናን ከመፍራት የሚመነጨው ግን ለዜጎች፣ በተለይም በመዲናዋ ለሚገኙት ሎንዶነርስ ሥጋት፣ ለአገሪቷ ደኅንነት ክፍልም ፈተና ሆኗል፡፡

ዛሬ በነዳጅ ሀብቷ የበለፀገች ብትሆንም እ.ኤ.አ. ከ1939 በፊት የነበራት የሀብት ደረጃ ደሃ ከሚባሉት አገሮች ያሠልፋት ነበር፡፡ በ1700ዎቹ ለንግድ በሚዘዋወሩ ሰዎች በባህረ ሰላጤው ደሴት ላይ ተመሠረተችው ኳታር፣ አሁን ከባህረ ሳላጤው ሀብታም አገሮች በሀብቷ ከቀዳሚዎቹ ትሠለፋለች፡፡ 

Pages