ሃያ አንድ አገር አቀፍ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከኢሕአዴግ ጋር በተናጠል ወይም በጋራ ለመደራደር ለመወሰን ሰኞ መጋቢት 4 ቀን 2009 ዓ.ም. ያደረጉት ስብሰባ ባለመሳካቱ፣ በተናጠል ውይይት የሚያደርጉት ዕድል እየሰፋ መምጣቱ ተጠቆመ፡፡

​የፌዴራል መንግሥት የሕግ ምርምር፣ ሥልጠናና የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራምን በመቀላቀል በአንድ ተቋም ሥር አድርጎ ለመሥራት እየመከረ ነው፡፡ የመጀመሪያውን ምክክር ከባለድርሻ አካላት ጋር በሐርመኒ ሆቴል ጥር 15 ቀን 2009 ዓ.ም. አድርጓል፡፡ 

​የፖለቲካ ተንታኞች በኢሕአዴግ የምትመራው ኢትዮጵያ ካለፉት ሥርዓቶች በወረሰችው ፈላጭ  ቆራጭና  አምባገነናዊ ባህል፣ ሕገ መንግሥቷና ዝርዝር ሕጐቿ በሚሰብኩት ጠንካራና ጤናማ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መካከል የምትዋልል እንደሆነች ያስረዳሉ፡፡

​በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚመራ የላይኛው ሱሉልታ አሳታፊ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ፕሮጀክት፣ ጥር 10 ቀን 2009 ዓ.ም. በአዲስ ራማዳ ሆቴል ከባለድርሻዎች ጋር በተካሄደ የምክክር ዓውደ ጥናት ይፋ ሆነ፡፡

​‹‹እ.ኤ.አ. በ2040 በውኃ እጦት የሚሰቃዩ አሥር ተቀዳሚ አገሮች  የትኞቹ ናቸው?››

ጋዜጠኛና ጸሐፊው ዳንኤል ካሊናኪ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ናይል ቤዚን ኢንሺየቲቭ (ኤንቢአይ) እ.ኤ.አ. ከታኅሳስ 12 እስከ 16 ቀን 2016 በሩዋንዳ ኪጋሊ አዘጋጅቶት ለነበረው ክልላዊ የሚዲያ ሥልጠና ተሳታፊዎች ነው፡፡ 

Pages