የወረር ግብርና ምርምር ማዕከል በየዓመቱ ከውጭ አገር የሚገባውን አሥር ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለማስቀረት እየሠራሁ ነው አለ፡፡ በአገሪቱ ቆላማ ቦታዎች በተለይም በአፋር ክልል የሚገኙ ሰፋፊ የጥጥ እርሻዎች በሞቃት ወቅት ጥጥ፣ በቀዝቃዛው የምርት ወቅት ደግሞ ስንዴ እያፈራረቁ እንዲያመርቱ ማድረግ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የሚከተሉት ስትራቴጂ ነው፡፡

አቶ ካሊድ አደም

አቶ ካሊድ አደም ተወልደው ያደጉት አዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1991 የ16 ዓመት ልጅ ሳሉ ነበር፡፡ አሜሪካ ትኖር የነበረችው አክስታቸው ባመቻቸችላቸው ዕድል አሜሪካ ሄዱ፡፡

በአንዴ ከስድስት ሰው በላይ መያዝ በማይችለው የእንፋሎት (ስቲም) መታጠቢያ ክፍል ውስጥ በከፊል የተሸፈኑ ሴቶች ተደርድረዋል፡፡ ከሁለቱ በስተቀር የተቀሩት እርስ በርስ አይተዋወቁም፡፡ 

‹‹መቼም ገንዘቡ ካለቀ እኛም አለቅን ማለት ነው፤›› አሉ የሆስፒታሉ አልጋ ላይ ጋደም እንዳሉ፡፡ በግምት በ60ዎቹ መጀመርያ ላይ የሚገኙት እኚህ ሰው ኩላሊታቸው ሥራውን ካቆመ ዓመታት አስቆጥሯል፡፡ 

የለበሱት በዝናብ ርሧል፡፡ ችግኝ ለመትከል በተመረጠው በእንጦጦ ማርያም ጋራ ላይ የተገኙት ማልደው ነው፡፡ በግምት ሁለት መቶ የሚሆኑ በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የሚሠሩ ሰዎች ናቸው፡፡ 

ስለሥርዓተ ምግብ ያለው ግንዛቤ እያደገ ቢሆንም፣ ከውኃ እጥረትና ከአካባቢና የግል ንፅሕና መጓደል ጋር ተያይዘው የሚመጡ በሽታዎች 30 በመቶ ለሚሆነው መቀንጨር ምክንያት እንደሆኑ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የእናቶችና ሕፃናት ጤና ዳይሬክተር ኤፍሬም ተክሌ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

Pages