አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
  • የተመድ ሪፖርት በዓለም አሳሳቢ የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋ ተንሰራፍቷል ይላል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና የልማት ጉባዔ በየጊዜው ይፋ ከሚያደርጋቸው ጥናታዊ ሪፖርቶች መካከል የንድና የልማት ጉባዔ የተሰኘው ይጠቀሳል፡፡ የዚህ ዓመት ሪፖርትም ባለፈው ሳምንት በአፍሪካ ኅብረት ይፋ ተደርጓል፡፡

  • የኩባንያው ባለቤት ‹‹ተስፋ ቆርጫለሁ ተሸንፌያለሁ›› አሉ

 ለሰባት ዓመታት ያህል በጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ከመቶ ሺሕ ሔክታር  በላይ መሬት የእርሻ ቦታ በመያዝ የሜካናይዝድ ግብርናን ለማካሄድ ሲሞክር የቆየው የህንዱ ካሩቱሪ ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ ለቆ መውጣቱንና ኢንቨስትመንቱን ማቋረጡን ለሪፖርተር ይፋ አደረገ፡፡

ካፒቴን አበራ ለሚ የናሽናል አየር መንገድ ኢትዮጵያ ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡ ናሽናል አየር መንገድ (የቀድሞው ኤር ኢትዮጵያ) ከአሥር ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ የግል አቪዬሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ተሳትፎ በማድረግ ከሚጠቀሱ ኩባንያዎች መካከል ይመደባል፡፡

በአሁኑ ወቅት በርካታ ዓለም አቀፍ ብራንድ ያላቸው የውጭ ሆቴሎች በአዲስ አበባ ከተማ እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ አብዛኞቹም ከየማዕዘናቱ የሚመጡ የውጭ ዜጎችን ዒላማ ያደረገ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ አብዛኛው ደንበኞቻቸውም የውጭ ዜጎች መሆናቸው ዕሙን ነው፡፡

ከተመሠረተ ሦስት አሥርታትን ያጋመሰው የምሥራቅና የደቡብ አፍሪካ አገሮች የንግድና የኢንቨስትመንት ባንክ (በቀድሞው አጠራሩ ፍሪፈረንሺያል ትሬድ አክሰስ ባንክ- ፒቲኤ ባንክ)፣ ከረዥም ዓመታት ጉዞው አኳያ በአምስት ዓመታት ውስጥ ያሳየው ለውጥ በትልቁ ይዘከራል፡፡

በብርሃኑ ፈቃደ፣ ማሔ ደሴት ሲሼልስ

ራሱን በምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) የንግድና የልማት ባንክ በማለት ስያሜውን ያሻሻለው የቀድሞው ፒቲኤ (Preferential Trade Agreement- PTA Bank)፣ በዚህ ዓመት ጥር ወር ይፋ ባደረገው መሠረት ለሦስት ኩባንያዎች በአጠቃላይ የ60 ሚሊዮን ዶላር ብድር ጥያቄ ቀርቦት ሲመለከት ቆይቶ ፈቀደ፡፡

ሑድ ነሐሴ 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከአገሪቱና ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ባለሥልጣናት ጋር የተወያዩት የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታሮ ኮኖ፣ ከሰሜን ኮሪያ የኑክሌርና የሚሳይል ጥቃት ጀምሮ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና በሚታዩት የፀጥታ ሥጋቶች ላይ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር የሚስማማ አቋም እንዳላት አስታወቁ፡፡

Pages