​ኢሕአዴግ ለቅድመ ውይይት ከጠራቸው 22 ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል በአቶ  ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር)  የሚመራው የሰማያዊ ፓርቲ ቡድን የተገኘ ቢሆንም፣ በውይይቱ ላይ መሳተፍ የቻለው እስከ ሻይ ዕረፍት ድረስ ብቻ መሆኑን አስታወቀ፡፡

​በተለያዩ ሰዎች ስም የቡና ላኪነት የንግድ ፈቃድ በማውጣትና ከሌሎች ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመመሳጠር መንግሥትን ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ በማሳጣትና በአገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ፣ አምስት የቡና ነጋዴዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ታሰሩ፡፡

​የቂሊንጦ እስረኛ ማቆያን በማቃጠል የ23 ተከሳሾች ሕይወት በማጥፋትና 15 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ንብረት በማውደም ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸውን ተከሳሾች ክርክር፣ በዝግ ችሎት እንዲሆንለት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ፍርድ ቤትን ጠየቀ፡፡

​በቀድሞ የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ የኦፕሬሺን ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ በትረወርቅ ታፈሰ፣ በመንግሥት ላይ የ12.2 ሚሊዮን ብር ጉዳት በማድረስ ተጠርጥረው የሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

​  በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ የፋይናንስ የሥራ ሒደት ዳይሬክተርና የደንበኞች ግንኙነት አስተዳደር የሥራ ሒደት ዳይሬክተር፣ ባንኩን ከ276.6 ሚሊዮን ብር በላይ በማስመዝበር ተጠርጥረው ታሰሩ፡፡ 

ከ2000 ዓ.ም. እስከ 2007 ዓ.ም. ድረስ በነበሩት በጀት ዓመታት፣ መንግሥት ወደ ውጭ  ከሚላክ ቡና ሊያገኝ ይችል የነበረውን ከ77.6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወይም በወቅቱ ምንዛሪ ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ በማሳጣት የተጠረጠሩ የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎችና ቡና ነጋዴዎች ታሰሩ፡፡

Pages