በልዩ ልዩ ምክንያት መርዝ ጠጥተው ወይም በሐኪሞች ከታዘዘው በላይ መድኃኒት ወስደው ለከፋ የጤና መታወክ ለተዳረጉ ሕሙማን የተሟላ የሕክምና አገልግሎት የመስጠት አቅም ባለው ቴክሲኮሎጂ ኤንድ ሪሰርች ሴንተር በኩል፣ ቶክሲኮሎጂ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ፋኩልቲ እንደ አንድ የትምህርት ክፍል እንዲሰጥ ሐሳብ  ቀረበ፡፡

ለአየር ንብረት መዛባት የኢንዱስትሪው መበልፀግና የአኗኗር ዘይቤ እንደ ምክንያት ይነሳሉ፡፡ የአየር ንብረት መዛባቱ ደግሞ፣ ለመዛባቱ ምክንያት የሆኑ ሰዎችን ብሎም እንስሳትንና ዕፅዋትን እየጎዳ ነው፡፡

ከአራት አሠርታት በፊት የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና (በዘመኑ አጠራር ‹‹ሚኒስትሪ››) የሚቀበሉ አንድ የመንግሥት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በተዘጋጀላቸው የፈተና ጣቢያ ውስጥ ተቀምጠው የፈተናውን መጀመር በመጠባበቅ ላይ ነበሩ፡፡ 

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በሚቀጥሉት ዓመታት በተለያዩ ስድስት የሕክምና ዘርፎች የልቀት ማዕከል ሆኖ ለመሥራት የሚያስችለውን እንቅስቃሴ በማከናወን ላይ መሆኑን የኮሌጁ የትምህርትና የምርምር ምክትል ፕሮþስት ይናገራሉ፡፡  

የሰዎች ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እንዲሁም ከማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ጋር ተያይዘው ለሚከሰቱ ድንገተኛ የጤና እክሎች ፈጣንና ቀልጣፋ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ወሳኝ ቢሆንም፣ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳጊ አገሮች ቀላል አይደለም፡፡

Pages