አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ሰማያዊ ፓርቲ በአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ መስከረም 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ለማድረግ ባቀደው ሰላማዊ ሠልፍና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ለመስጠት፣ በሐራምቤ ሆቴል ጠርቶት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ባልታወቀ ምክንያት መከልከሉን አስታወቀ፡፡

ከገዥው ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እየተደራደሩ የሚገኙ 12 ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመደራደሪያ ሐሳባቸውን በጋራ ለማቅረብና ለመደራደር ወሰኑ፡፡

አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን፣ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አዲሱ አምባሳደር

አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን ነሐሴ 21 ቀን 2009 ዓ.ም. በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል፡፡ የደርግ መንግሥትን ከሥልጣን ለማውረድ በኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢሕዴን)፣ ደርግ ከወደቀ በኋላ ደግሞ ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) በተባለው ውስጥ ሆነው ታግለዋል፡፡

በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጋር እሑድ ነሐሴ 7 ቀን 2009 ዓ.ም. በመብራት ኃይል አዳራሽ ውይይት ለማድረግ ያስገቡትን የዕውቅና ጥያቄ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምላሽ ባለመስጠቱ ምክንያት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) ዕቅዳቸውን መሰረዛቸውን አስታወቁ፡፡

ከዋናው ድርድር አስቀድሞ በርካታ ወራትንና አሰልቺ ውይይቶችን ያለፈው የገዥው ፓርቲና የ16 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ድርድር ባለፈው ሳምንት ተጀምሮ፣ በመጀመርያው ዙር በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ውስጥ አዳዲስ አንቀጾች ለማካተትና ያሉትን ለማሻሻል ስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡

  • ፕሮፌሰር በየነ የኢሶዴፓ ሊቀመንበር ሆኑ

ቅዳሜ ሐምሌ 8 ቀን 2009 ዓ.ም. 13ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን 6 ኪሎ አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤቱ ያከናወነው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)፣ ዶ/ር ሚሊዮን ቱማቶን ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንዲመሩት ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ፡፡

Pages