ዘንድሮ በ2009 ዓ.ም. ሰኔ 30 ላይ የተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የአገሪቱ ሃምሳ ስድስተኛው የበጀት ዓመት ነበር፡፡ ከሐምሌ 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ አዲሱን ማለትም 57ኛውን የበጀት ዓመት ጀምረናል፡፡ 

ቁርጥ ግብር፣ ለማስገበር አስቸጋሪ የሆኑ ገቢ ላይ ይተገበራል፡፡ በቁርጥ የሚጣል ግብር መጠን በተጠና ግምት ይሰላል፡፡ ግብር ተማኙና ሰብሳቢው ባለሥልጣን ትክክል ነው ብሎ የሚያስበውን ግብር በግምትም ቢሆን ለማወቅ የተለያዩ መረጃዎች ላይ ይመሠረታል፡፡ 

የዛሬ 20 ዓመት (በ1989 ዓ.ም.) በዛሬው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ፋካልቲ፣ በያኔው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ኢንስቲትዩት በጋዜጠኝነት ትምህርት ላይ ሳለን አንድ አሰቃቂና አስደንጋጭ አደጋ ደርሶ ነበር፡፡ 

መከላከያ ሠራዊት ለአገር ያለው ጠቀሜታና አስፈላጊነት በምንም ሁኔታ ለጥያቄ አይቀርብም፡፡ የመንግሥትና የአገር ሕልውና፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ የልማት ሥራዎችና ግዙፍ ፕሮጀክቶች ደኅንነት ያለ መከላከያ ሠራዊት ከለላ ሕልውናቸው አደጋ ውስጥ ነው፡፡

እነሆ መንገድ ከመገናኛ ወደ ስድስት ኪሎ። የጎዳናው ጭብጥ ተደጋጋሚ ነው። ሕይወት ቀለም ያለቀባት ትመስላለች። በመንጋ ቅርፅ አሠልፋ የምትነዳው እልፍ ነው። 

Pages