የፌዴራል መንግሥት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር በውክልና የወሰደው የገቢዎች ባለሥልጣን፣ በድጋሚ ወደ ከተማው አስተዳደር እንዲመለስ ተወሰነ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለሥልጣንን በቢሮ ደረጃ ሊያዋቅር መሆኑ ታውቋል፡፡

‹‹የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ›› በሚባል ስያሜ የሚቋቋመው ተቋም በካቢኔ አባል የሚመራ ይሆናል ተብሏል፡፡

መንግሥት በ2010 ዓ.ም. ከ353 ሺሕ በላይ ቤቶችን በገጠራማ አካባቢዎች ለመገንባት መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በትግራይ፣ በቤንሻንጉልና በሐረር ክልሎች ግንባታ የሚካሄድባቸው የገጠር ማዕከላት መለየታቸውም ተገልጿል፡፡

  • አዳዲስ ጥያቄዎች በኢንዱስትሪ ዞን ይስተናገዳሉ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ2007 ዓ.ም. በፊት ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ግንባታ መሬት የጠየቁ ኩባንያዎች በተናጠል እንዲስተናገዱ፣ ከ2007 ዓ.ም. ወዲህ መሬት የጠየቁ ኩባንያዎች ደግሞ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን በሚያለማው ኢንዱስትሪ ዞን እንዲስተናገዱ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ የሚያገኘው ልዩ ጥቅምን አስመልክቶ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ የመጀመርያውን ምክክር አካሄዱ፡፡

Pages