​ከኃላፊነት የሚነሱ የአገርና የመንግሥት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የምክር ቤት አባላትና ዳኞች የሚያገኟቸው መብቶችና ጥቅሞችን የሚወስነው አዋጅ ላይ ማሻሻያ በማድረግ፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጥቅማ ጥቅም ከፍ ሊል ነው፡፡

​ግሎባል ፈንድ በመባል የሚታወቀው ኤድስን፣ ሳንባ ነቀርሳንና ወባን ለመዋጋት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው  ድርጅት ሀብትን በሚገባ ለመጠቀም፣ ግሎባል ፈንድና እሱ የሚወክላቸው የሥራ ኃላፊው በነፃነት በኢትዮጵያ እንዲንቀሳቀሱ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡

ሰኞ ጥር 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በጽሕፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ከረጅም ጊዜ በኋላ በተሰጠው በዚህ መግለጫ ጋዜጠኞች አንገብጋቢና በቅድሚያ ምላሽ ያስፈልጋቸዋል ያሉዋቸውን ጥያቄዎች አቅርበዋል፡፡ 

​አዋጅ ወጥቶለትና መዋቅር ተዘጋጅቶለት በሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተግባራዊ ሊደረግ የነበረው ማኅበራዊ የጤና መድን ሥራ ላይ  እንዳይውል እክሎች እንደገጠሙት፣ በዚህም ምክንያት በሌላ አሠራር ሊተካ እንደሚችል የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ለፓርላማው ይፋ አደረጉ፡፡

Pages