​ገዢው ፓርቲን ጨምሮ ከጥቂት ሳምንት በፊት የቅድመ ድርድር ውይይት የጀመሩት 22 አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዓርብ የካቲት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ውይይት አደረጉ፡፡ በውይይቱ ወቅት አሁንም ያልተፈቱ ልዩነቶች  ተንፀባርቀዋል፡፡

የግብፅ ፕሬዚዳንት በኬንያ ባደረጉት ይፋዊ ጉብኝት አገራቸው በዓባይ ወንዝ ጉዳይ ከተፋሰሱ አገሮች ጋር ለመተባበር፣ ከአባልነት ራሷን ካገለለችበት የናይል ቤዚን ኢንሼቲቭ ጋር ደግሞ በድጋሚ ለመነጋገር የሚያስችል የተለሳለሰ አቋም አሳዩ፡፡

ግሎቤሌክና ኮንቲንጀንት ቴክኖሎጂ የተባሉ ሁለት የእንግሊዝ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ በመገንባት፣ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሽያጭ ለማቅረብ ከመንግሥት ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን አስታወቁ፡፡

Pages