የአገሪቱ ሁሉም ባንኮች የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ፡፡ ለባንኮች ያልተጠበቀ ነው የተባለው የቅርንጫፎች ማስፋፋትና ማጠናከራቸው፣ የአስቀማጮችን ቁጥር ከ24 ሚሊዮን በላይ እንዲደርስ ማስቻሉ ተመልክቷል፡፡

  • በ2009 በጀት ዓመት ከ5.4 ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቦለት ነበር

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን በ2010 በጀት ዓመት 101 ፕሮጀክቶችን ለመተግበር መነሳቱንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም የ6.38 ቢሊዮን ብር በጀት እንዳፀደቀለት አስታወቀ፡፡

አቢሲኒያ ባንክ የ2009 ዓ.ም. በጀት ዓመት የሰጠው የብድር መጠን በ73.3 በመቶ በማሳደግ 14.1 ቢሊዮን ብር ማድረሱን ገለጸ፡፡ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ ደግሞ ከ 20.7 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ገናና ስም ከነበራቸው የአገር ውስጥ ተቋራጮች በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት መካከል አንዱ አኪር ኮንትራክሽን አክሲዮን ማኅበር ባለቤትነት ሙሉ ለሙሉ በሽያጭ ተላለፈ፡፡   

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ማቋቋሚያ አዋጅ ሰሞኑን ለሁለተኛ ጊዜ እንዲሻሻል መደረጉ ይታወቃል፡፡ የማቋቋሚያ አዋጁ እንደገና እንዲሻሻል የተፈገለው የአገሪቱን የቡና ዘርፍ ብቻም ሳይሆን ወጪ ንግዱን ችግሮች ለማሻሻል ከተጀመረው እንቅስቃሴ ጋር  በማያያዝ ለውጥ እንዲመጣ በማሰብ ነው፡              

ዘመናዊ የባንክ አገልግሎትን ለማስፋፋት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ኢትስዊች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የሁሉንም ባንኮች የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በማስተሳሰር በአንድ ላይ መስጠት የሚያስችለውን አዲስ አገልግሎት ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ከአዲስ አበባ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ሊተገበሩ ይገባቸዋል ተብለው ከሚታሰቡ መሠረት ልማቶች መካከል አንዱ የሆነው፣ የተሽከርካሪዎች መናኸሪያና ከዚሁ ጋር የተቀናጀ አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከሎች ናቸው፡፡ 

Pages