በአገር ውስጥ የእግር ኳስ ውድድሮች ስኬታማ መሆን የቻለው ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ፣ በአፍሪካ መድረኮች የመሳተፍ ዕድል ቢያገኝም በውድድሮቹ ላይ ከመሳተፍ ባሻገር እምብዛም የሚጠቀስ ስኬታማ ጉዞ ሲያደርግ አልተስተዋለም፡፡

​ለ14ኛ ጊዜ በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎችና ተጋባዥ ተቋማት መካከል የሚከናወነው የስፖርት ውድድር፣ የካቲት 26 ቀን 2009 ዓ.ም. በመቻሬ ሜዳ ኮርፖሬት ሴንተር ግቢ ተጀምሯል፡፡

​‹‹የኢትዮጵያ የጃዝ አባት››  በመባል የሚታወቀው አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ፣ የኢትዮጃዝ ኮንሰርት ከለንደኑ እስቴፕ ባንድ ጋር በመቀናጀት የካቲት  11 ቀን 2009 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡

​በግብርና ዘርፍ፣ በምግብና በመጠጥ፣ በፕላስቲክ እንዲሁም በማሸጊያ ቴክኖሎጂ እንዲሁም በጥሬ ዕቃዎች ላይ ያነጣጠረውና ‹‹አግሮ ፉድ ፕላስት ፓክ ኢትዮጵያ›› የተሰኘ የንግድ ዓውደ ርዕይ ከጥር 26 እስከ ጥር 28 ቀን 2009 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ 

​ኢትዮጵያ ከ1950ዎቹ ጀምሮ በአትሌቲክስ በተለይም በኦሊምፒክ ያሳየችው ድንቅ ክንውን ለዘመናት በታሪክ ምኅዳር፣  በዓለም አደባባይ ደምቃ እንድትታይና በተለይ ‹‹ኢትዮጵያ ማናት?›› ለሚለው ጥያቄ መልስ በመስጠት የራሱ ድርሻ ሲወጣ ቆይቷል፡፡

Pages