አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ምን የት?

የሥዕል ዐውደ ርዕይ

ዝግጅት፡‑ የሠዓሊ ዳዊት አድነው ሥራዎች ‹‹ሒደት›› በተሰኘ የሥዕል ዐውደ ርዕይ ይታያሉ፡፡ በዐውደ ርዕዩ መዝጊያ ግጥም በሙዚቃ በኤፍሬም ሥዩም፣ ደምሰው መርሻ፣ ምልዕቲ ኪሮስና ሌሎችም ገጣሚዎች ይቀርባል፡፡

ቀን፡‑ ከጥር 5 እስከ 12 ቀን 2009 ዓ.ም.

ሰዓት፡‑ 12፡00

ቦታ፡‑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም

የብርሃንና ሰላም 95ኛ ዓመት

ዝግጅት፡‑ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት 95ኛ የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የፎቶግራፍና ዘጋቢ ፊልም ዐውደ ርዕይ ይታያል፡፡ የፓናል ውይይትና የተቋሙ ሦስት ፕሮጀክቶች ምርቃትም ይካሄዳል፡፡ አንዱ ፕሮጀክት የተቋሙ ባለሰባት ፎቅ የኅትመት ማሠልጠኛ አካዴሚ እንደሆነ ተቋሙ ለሪፖርተር የላከው መግለጫ ያስረዳል፡፡

ቀን፡‑ የዐውደ ርዕይ መክፈቻ ጥር 20 ቀን 2009 ዓ.ም.

ቦታ፡‑ በተቋሙ ቅጥር ግቢ