ታዳጊዎች በዓድዋ ከተማ 121ኛውን የዓድዋ ድል በዓል ሲያከብሩ

ከሙታን ጋር ፎቶ መነሳት የሚያስችለው አፕልኬሽን 

የዚህ ሳምንት ማብቂያ የሜትሮ ዘገባ እንደሚያመለክተው አንድ የደቡብ ኮሪያ ኩባንያ ሰዎች በሕይወት ከሌሎች ዘመዶቻቸው ጋር ሆነው ፎቶግራፍ መነሳት የሚያስችላቸውን ሶፍትዌር ሠርቷል፡፡ ይህ ሶፍትዌር ‹‹ዊዝ ሚ›› የሚሰኝ ሲሆን ቤተሰብ ወይም ጓደኛቸውን የማጣት ሐዘን አልወጣ ያላቸውን እንደሚረዳ ተገልጿል፡፡

*********

ከለንደን ወደ ሳንፍራንሲስኮ ሊደረግ የነበረው በረራ በአይጥ ተስተጓጎለ

በብሪቲሽ ኤርዌይስ 285 ከለንደን ወደ ሳንፍራንሲስኮ ለመጓዝ መቀመጫቸውን ይዘው ለበረራ እየተዘጋጁ የነበሩ መንገደኞች ድንገት ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ተደገ፡፡ መንገደኞቹ እንዲወርዱ የተደረገው አንድ ትንሽዬ ዓይጥ አውሮፕላን ውስጥ በመገኘቷ ሲሆን ይህ ሁኔታ በረራው ለአራት ሰዓት እንዲዘገይ አድርጓል፡፡ በመጨረሻም ተጓዦቹ ከሌላ አውሮፕላን ውስጥ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ አንዳንድ መንገደኞች በሁኔታው ከመበሳጨት ይልቅ መቀለድን መርጠዋል፡፡ አንዲት መንገደኛ ‹‹አይጧ የአማሪካ ቪዛ ስለሌላት ነው ይህ ሁሉ የሆነው›› ማለቷን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

********

ጩኸት በሚበዛበት ከተማ የሚኖሩ ለመስማት ችግር የተገለጡ ናቸው ተባለ

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዓርብ ዕለት እንደዘገበው የድምፅ ብክለት ባለባቸው ከተሞች የሚኖሩ ለመስማት ችግር የተጋለጡ ናቸው፡፡ በተመሳሳይ ቀን የወጣ የከተሞች የድምፅ ብክለት ሪፖርት እንደሚያሳየው በድምፅ ብክለት 50 የሚሆኑ የዓለም ከተሞች ተለይተዋል፡፡ ከእነዚህ ከተሞች የቻይናዋ ጓንዡ፣ የህንዷ ደሊህ፣ የግብጿ ካይሮ እንዲሁም የቱርኳ ኢስታምቡል ቀዳሚውን ደረጃ ይይዛሉ፡፡ በተቃራኒው የድምፅ ብክለት ችግር ከሌለባቸው ከተሞች ዙሪክ፣ ቬና፣ ኦስሎና ሙኒክ ቀዳሚውን ቦታ ይዘዋል ምንም እንኳ የከተማ ሕይወት ለመስማት ችግር ያጋልጣል ባይባልም የድምፅ ብክለትና የመስማት ችግር ትልቅ ቁርኝት እንዳላቸው ጥናቱ ያረጋግጣል፡፡፡