አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

አደገኛው አሳ

ሻርክና ባራኩዳ የሚባሉ የአሳ ዝርያዎች በአደገኝነታቸው ቢታወቁም፤ የትኞቹም ቢሆኑ ከትንሹ ጨው አልባ (ሐይቅና ወንዝ) ውኃ ውስጥ ነዋሪ ከሆኑት የደቡብ አሜሪካ አሳዎች በአደገኛነታቸው የሚወዳደሩ አይሆኑም፡፡ እኒህ አደገኛ አሳዎች ፒራንህ፣  ካራቤ እና ፒራይ ይባላሉ፡፡ የትኛውም የየብስ ላይ እንስሳ ምንም ትልቅ ቢሆን ከነዚህ አነስተኛ እንስሳት አደጋ ሊጠበቅ አይችልም ተብሎ ይታመናል፡፡

ትልቅ አፍና ወጣ ያለ ግንጭል ሲኖራቸው በያንዳንዱ ግንጭል ውስጠ ለነሱ አነስተኛ አቅም የበዛ የሚመስል በጣም የሰሉ ጥርሶች አላቸው፡፡ በአብዛኛው በቡድን ሆነው ያጠቃሉ፡፡ እነሱ ያጠቁት እንስሳ ምንም ዓይነት ሥጋ ሳይኖረው በአጥንቱ ብቻ ይቀራል፡፡ እርስ በርሳቸውም ሳይተዛዘኑ መበላላታቸውም ተዘግቧል፡፡ ሊደርሱበት የቻሉትን የታዳኝ አካል ክፍል በመብላት ጀምረው ያለምንም ርኅራኄ ከውኃ ውጪ ያለውን ክፍል ወጥተው እስከመብላት ይደርሳሉ፡፡ በአሳ መንጠቆ ከአሳው አፍ ለማላቀቅ ጥረት ያደረጉ ሰዎችም በእነዚሁ አደገኛ አሳዎች ጣታቸው መተልተሉ ተዘግቧል፡፡

  • ማንይንገረው ሽንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004 ዓ.ም.)