አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ወቅታዊው መረጃ

የአሜሪካ መንግሥት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሽብር ጥቃት ዕቅዶች በመኖራቸው፣ የአሜሪካ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ካወጣው መግለጫ የተወሰደ፡፡ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ሰኞ ኅዳር 13 ቀን 2008 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አይኤስ፣ አልቃይዳ፣ ቦኮ ሐራምና ሌሎች አሸባሪ ቡድኖች በተለያዩ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለማድረስ እያሴሩ ናቸው ብሏል፡፡ የታቀዱት የሽብር ጥቃቶች የተለያዩ ሥልቶችን እንደሚጠቀሙ የገለጸው የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት፣ አሸባሪዎቹ መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ የጦር መሣሪያዎችን በመጠቀም የመንግሥትና የግል ተቋማት ላይ ማነጣጠራቸውን አስታውቋል፡፡ እንደ ምሳሌም በዴንማርክ፣ በፈረንሣይ፣ በማሊ፣ በናይጄሪያና በቱርክ የተፈጸሙ ጥቃቶችን አስታውሷል፡፡ በሕዝብ የተጨናነቁ ሥፍራዎች፣ የስፖርት ውድድሮች፣ የገበያ ማዕከላትና አውሮፕላን ማረፊያዎች የአሸባሪዎች ዒላማ ሊሆኑ ስለሚችሉ፣ ዜጐች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡ በምሥሉ ላይ የሚታዩት የኒውዮርክ ፖሊሶች በአውሮፕላን ማረፊያዎችና በባቡር ጣቢያዎች ጥበቃ ሲያደርጉ ነው፡፡