አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ዓሳ በአቮካዶ

ጥሬ ዕቃዎች

 • 450 ግራም ቴላፒያ ፍሌቶ ዓሳ
 • ዘይት ለመጥበሻ
 • ጨውና ቁንዶ በርበሬ
 • ጥሬ ዕቃዎች ለሳልሳ
 • 2 መካከለኛ አቮካዶ
 • 2 መካከለኛ ፍሬ ቲማቲም
 • 1 የፈረንጅ ቃሪያ
 • 2 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
 • (1/2) ግማሽ የሻይ ማንኪያ ሚጥሚጣ (ዛላ ወይም የተፈጨ)
 • 1 የሻይ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ
 • 3 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
 • ጨውና ቁንዶ በርበሬ

አዘገጃጀት

 1. ዓሳውን በደንብ አጥቦ እሾሁን ማውጣትና በጨውና ቁንዶ በርበሬ መቀመም፤
 2. በመጥበሻ ውስጥ አግሎ ዓሳውን መጥበስ፤
 3. አቮካዶውን በትንንሹ መቆራረጥ፤
 4. የፈረንጅ ቃሪያውን ቆራርጦ በመጥበሻ ዘይት አግሎ መጥበስና አውጥቶ ማቀዝቀዝ፤
 5. ነጭ ሽንኩርቱን በደንብ ማድቀቅ፤
 6. በጎድጓዳ ሰሀን አቮካዶውን፣ የተጠበሰውን ቃሪያና ነጭ ሽንኩርቱን መጨመርና ማደበላለቅ፤
 7. ቲማቲሙን እንዲሁ በደቃቁ ከትፎ ወደ አቮካዶው ውስጥ መጨመር፤
 8. ሎሚ ጭማቂ፣ ሚጥሚጣ ጨውና ቁንዶ በርበሬ አደበላልቆ የተጠበሰው ዓሳ ላይ አድርጎ ማቅረብ፡፡
 • ጆርዳና ኩሽና ‹‹የምግብ አዘገጃጀት›› (2007)