የቀይ ሥጋና የካሮት ለጋ ጥብስ

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች

  • 175 ግራም ድንች
  • 225 ግራም ካሮት
  • ¼  ቀይ ሽንኩርት
  • 175 ግራም ቀይ የጥብስ ሥጋ
  • 300 ሚሊ ሊትር ውኃ

አዘገጃጀት

  • ኦቨኑን በ180 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ማጋል፣ ካሮት ፣ ድንችና ቀይ ሽንኩርቱን ከትፎ በድስት ማድረግ
  • ቀዩን ሥጋ በአራት ማዕዘን ቅርጽ መክተፍ
  • ሥጋ፣ ካሮት፣ ድንች፣ ሽንኩርትና ውኃውን ድስቱ ውስጥ ጨምሮ ኦቨን ውስጥ በመክተት ከ1-1½ ሰዓት ወይም ሥጋውና አትክልቶቹ በደንብ እስኪበስሉ መቀቀል
  • የተቀቀለውን በመፍጨት መመገብ

ሜላት ዮሴፍና ህሊና በለጠ፣ ‹‹ጣዕም ያላቸው የሕፃናት ምግቦች ለመጀመሪያዎቹ 1000 ቀናት›› (2009)