አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

የቆስጣ አሠራር

ጥሬ ዕቃዎች

 1. አንድ እስር ቆስጣ /ከሁለት እስከ ሦስት ደቂቃ በስሎ የቀዘቀዘ/
 2. ሁለት ራስ ቲማቲም
 3. አንድ ራስ ቀይ ሽንኩርት /የተከተፈ/
 4. ሁለት ፍሬ ነጭ ሽንኩት /የደቀቀ/
 5. አንድ የሻይ ማንኪያ የሾርባ ቅጠል /ፐርስሊ/
 6. ሦስት የሾርባ ማንኪያ የአትክልት /የሱፍ/ ወይራ ዘይት
 7. ሁለት ፍሬ ሎሚ /ጭማቂ/
 8. ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው
 9. ግማሽ የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
 10. ሁለት ዳቦ

አዘገጃጀት

 • ተቀቅሎ የቀዘቀዘውን በግርድፍ በመክተፍ ከተዘጋጀው ቲማቲም፣ ቀይና ነጭ ሽንኩርት እንዲሁም ፐርስሊ ጋር መቀላቀል፣
 • የሎሚውን ጁስ ከዘይት፣ ጨውና ቁንዶ በርበሬ ጋር በማደባለቅ በተዘጋጀው ሰላጣ ላይ ጨምሮ ማዋሃድ
 • በተዘጋጀው ሰሀን ላይ በማድረግ ከዳቦ ጋር መመገብ፤