አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

የብርቱካን ዳቦ

 

 • ሦስት የሻይ ማንኪያ የዳቦ እርሾ
 • ሁለት ብርጭቆ ውኃ
 • አንድ የቡና ስኒ የብርቱካን ውኃ
 • አንድ የቡና ስኒ የተፈገፈገ የብርቱካን ልጣጭ
 • አንድ የቡና ስኒና ሁለት የሾርባ ማንኪያ ስኳር
 • አንድ የሻይ ማንኪያ ጨው
 • ሦስት የሾርባ ማንኪያ የቀለጠ ማርገሪን
 • ሦስት ብርጭቆ ከአንድ የቡና ስኒ ፍርኖ ዱቄት
 • አንድ እንቁላል

አሠራሩ

 1. እርሾውን ለብ ባለ በግማሽ ብርጭቆ ውኃ መበጥበጥ
 2. በቀረው ውኃ የብርቱካን ጭማቂ መቀላቀል
 3. ስኳሩን፣ ጨውን፣ የብርቱካን ልጣጭና ማርገሪኑን እተቀላቀለው ውስጥ መጨመር
 4. ዱቄቱን መንፋትና፣ 2 ብርጭቆ መጨመርና ደህና አድርጐ ማሸት
 5. እንቁላሉንና እርሾውን መጨመርና ደህና አድርጐ ማሸት፡፡
 6. የቀረውን አንድ ብርጭቆ ከአንድ የቡና ስኒ ዱቄት ጨምሮ ከአምስት ደቂቃ እስከ ስምንት ደቂቃ ማሸት
 7. ኩፍ እስኪል ድረስ ከድኖ ማስቀመጥ
 8. የሚጋገርበትን ዕቃ ዘይት መቀባትና ማሰናዳት
 9. ሊጡ ኩፍ ካለ በኋላ ማሸትና እሁለት ቦታ ቆርጣ መጋገሪያ ውስጥ መጨመር
 10.  ኩፍ እስኪል ድረስ ከድኖ ማስቀመጥ
 11.  የሚጋገርበትን ምድጃ ማጋል
 12.  ኩፍ ሲል መክተትና እስከ አርባ አምስት ደቂቃ ያህል ማብሰል
 • ገነት አጥናፉ ‹‹የቤት መሰናዶ በመልካም ዘዴ›› (1955)