አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

የተጋገረ ዓሳ (ቤክድ ፊሽ) ለ3 ሰው

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች

 • 600 ግራም ናይል ፐርች
 • 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ፊሽ ስቶክ
 • 2 መካከለኛ ጭልፋ ቢሻሜል ሶስ
 • 3 የእንቁላል አስኳል
 • 1 መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) ቺዝ
 • 3 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ
 • 3 የሾርባ ማንኪያ ክሬም

አዘገጃጀት

 1. ዓሳው ታጥቦ ከፀዳ በኋላ በቅቤ የተቀባ ድስት ውስጥ ማድረግ፤
 2. ፊሽ ስቶክ ጨምሮ ማንተክተክ፤
 3. መካከለኛ ሙቀት ባለው የዳቦ መጋገሪያ ውስጥ መጋገር፤
 4. ከበሰለ በኋላ ዓሳውን አውጥቶ ሌላ ዕቃ ላይ ማድረግ፤
 5. ቢሻሜል ሶሱን ለብቻ መጣድ፤
 6. አስኳሉን ጨምሮ መቀላቀል፤
 7. ከእሳቱ ማውጣትና ግማሹን ቺዝ ጨምሮ ማውረድ፤
 8. ቅቤና ክሬም አንድ ላይ መምታት፤
 9. ቀደም ሲል ዓሳው የተንተከተከበትን መረቅ ካጠለሉ በኋላ የተዘጋጀውን ክሬምና ወተት ዓሳው ላይ አፍስሶ የቀረውን ቺዝ ላዩ ላይ መነስነስ፤
 10.  በአነስተኛ ሙቀት ላይ ለትንሽ ጊዜ አብስሎ ማውጣት፤
 11.  በዝርግ ጭልፋ በጥንቃቄ አውጥቶ ማቅረብ፡፡
 • ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) ­‹‹የውጭ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2002)