የታመሰ ሥጋ በተመታ ቅቤ (ኩርፍ) - ለ3 ሰው

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች

 • ግማሽ ኪሎ ግራም የታላቅ ወይም የጭቅና ሥጋ
 • 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) በጣም ደቆ የተከተፈ ቃርያ
 • 1 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
 • 4 የሾርባ ማንኪያ ለጋ ቅቤ
 • 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
 • 1 የሻይ ማንኪያ ጨው

አዘገጃጀት

 1. ቀይ ሽንኩርቱን፣ ጨዉንና አንድ የሾርባ ማንኪያ ቅቤ ደባልቆ በነጩ ማቁላላት፤
 2. እንደተቁላላ ቃርያና ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ በጣም ሳይበስል ማውጣት፤
 3. የቀረውን ቅቤና አዋዜ ለብቻ ነጭ እስከሚሆን መምታት፤
 4. ለገበታ ሲቀርብ ሥጋውን ከተዘጋጀው ሽንኩርት፣ ቃርያ፣ ጨውና ቁንዶ በርበሬ ጋር አመስ፣ አመስ ካደረጉ በኋላ አውጥቶ የቅቤ ኩርፉን ወይም የተመታውን ቅቤ ላዩ ላይ በማፍሰስ ማቅረብ፡፡     
 • ደብረወርቅ አባተ “የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት” (2003)