አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

የንግሥት ዘውዲቱ ንግሥና ያደመቁት ሙዚቀኞች

ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ በነገሡበት መስከረም 17 ቀን 1909 ዓ.ም. በዓለ ሢመታቸው ሲከበር በዘመናዊ ሙዚቃ መሣርያዎች የተጫወቱት ኢትዮጵያውያን (ፎቶ በኤ. ኤን. ሚራዞፍ)

*****

እናትና ዕድሜ

ዝናቡ ይዘንባል..... . . . . . . . . . . .

በር ላይ ቆሜያለሁ፤

የደጁ ወጨፎ ያንዘፈዝፈኛል፣

ብልጭታ - መብርቁ፣ ከሰማዩ ጋራ፣ ከመንደሩ ጋራ፣ ይሰነጥቀኛል፡፡

አወይ እናት ማጣት!

አይ ልጅ መሆን መጥፎ፤

ዛሬም ባምሳ ዓመቱ፣ በደመነ ቁጥር፣ በዘነበ ቁጥር፣ ደጃፍ ተደግፎ፤

[አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ሔይኒከን ኢትዮጵያ የ30 ሚሊዮን ብር የስፖንሰርሽፕ ስምምነት አደረጉ]

ምን መብረቅ ቢወርድ፣ ምን ቆፈን ቢይዘው፤

‹‹ደጃፍ ላይ አትቁም፣ መብረቅ ትጠራለህ፣

ወጨፎ ይመታሀል፣ ለሊት ታስላለህ፡፡››

ካላለችው እናቱ፤

አይገባም ከቤቱ፡፡

ይኸው ክረምት መጣ፣ ዝናቡ ዘነበ፣

መብረቁ ይወርዳል፣

አድባር ይታረሳል፤

በር ላይ ቆሜያለሁ፤

ሞቴ ላይ ቆሜያለሁ፡፡

ከቆፈኑ በላይ፣

ከመብረቁ በላይ፣ . . .ሳጣሽ ያስፈራኛል፤

እማ ‹‹ግባ›› በዪኝ፣ ድምጽሽ ያድነኛል፡፡

(በድሉ ዋቅጅራ፣ ሚያዝያ፣ 2008)

*****

ቻይና ብሔራዊ መዝሙሯ ከተፈቀደው ፍጥነት ውጪ እንዳይዘመር ሕግ አወጣች

የአገሪቱ ብሔራዊ መዝሙር እግዲሁ ባዘቦትና በማንኛውም ሁኔታ መዘመሩ አግባብ አይደለም ያለችው ቻይና አዲስ ሕግ ማውጣቷን ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡ አዲሱ ሕግ እንደሚለው፣ የአገሪቱ ብሔራዊ መዝሙር መዘመር ያለበት ሕጉ ላይ በተጠቀሰው ፍጥነት ብቻ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ቀደም ቻይና ብሔራዊ መዝሙሯ ሠርግና የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ እንዳይዘመር ማገዷ ይታወቃል፡፡ ቻይና ይህን ያደረገችው እ.ኤ.አ. 2014 ላይ ሲሆን፣ መዝሙሩ መዘመር ያለበት ስፖርታዊ ዝግጅቶችና ከዲፕሎማሲያዊ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ እንደሆነ በሕጉ ተመልክቷል፡፡

****

እንዲህ ነው መዘነጥ

አየርላንድ ባለሙን በተባለ አካባቢ ከሚገኝ መካነ አራዊት ያመለጠው ጥንቸል መሰል እንስሳ እንዲህ ዘና እያለ መራመዱ አካባቢው ላይ የነበሩ ሰዎችን አስገርሞ ነበር፡፡ ‹‹እንስሳው ሲጋራ ይዞ ዘና እያለ ነው›› የሚለው ሐሳብ ብዙዎችን አስገርሞም ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን እንስሳው እንደ ሲጋራ በአፉ የያዘው እንደ መፋቂያ ያለ እንጨት መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ ከእንስሳው አረማመድና ሁለንተናዊ ሁኔታ የተነሳ ሰዎች በነገሩ መገረማቸውን ቀጥለው እንደበር ተዘግቧል፡፡  

 

በኡጋንዳ ጎዳና ላይ የሸናው ወጣት ቅጣት

በአዲስ አበባ ዋና ዋና ጎዳናዎች እንዲሁም በሰፈሮች ውስጥ ለውስጥም በየጥጋጥጉ ሽንታቸውን የሚሸኑ መመልከት እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ሰዎቹ የሚሸኑበትን አካባቢ ንፅሕናና የማኅበረሰቡንም ጤና እየበከሉ ስለመሆናቸውም ልብ የሚሉትም አይመስልም፡፡ እነዚህ ሰዎች ላይ አንዳች ዕርምጃ ሲወሰድም አይታይም፡፡ በምድረ ኡጋንዳ ከሰሞኑ የተሰማው ዜና ግን መንገድ ላይ የሚፀዳዱ ሰዎችን እንዴት መቅጣት እንደሚቻል ያስተማረ ነው፡፡ የ23 ዓመቱ ሞተረኛ ስቲቨን ሴንዴዳዬ ባለፈው ሳምንት ሽንቱን በውኃ ፕላስቲክ ውስጥ ሽንቶ ትቦ ውስጥ ሲወረውር እጅ ከፍንጅ መያዙን ዘኒው ቪዥን ኡጋንዳ ዘግቧል፡፡ ስቲቨን ፍርድ ቤት ቀርቦ ጥፋተኝነቱን ያመነ ሲሆን፣ ለ30 ሰዓታት የማኅበረሰብ አገልግሎት እንዲሰጥ ተበይኖበታል፡፡