የአረንጓዴ ላዛኛ አሠራር

ግብዓቶች

 • ሁለት ኩባያ ፉርኖ ዱቄት፣
 • ሁለት ትልልቅ እንቁላል፣
 • አምስት የሾርባ ማንኪያ በስሎ የተጨመቀና የተፈጨ እስፒናች፣
 • ትንሽ ውኃ፣
 • ስጎ፣
 • ባሽመል፣
 • አምስት የሾርባ ማንኪያ ፎርማጆ፣
 • ጨው እንዳስፈላጊነቱ

 አዘገጃጀቱ እንደሚከተለው ነው፤

 • ዱቄቱን በጠረጴዛ ላይ ነፍተን ጨው መጨመር፣
 • ዱቄቱን ስብስብ አድርገን መሀሉን ከፍተን እስፒናች እንቁላል አስፈላጊ ከሆነም ውኃ ጨምረን ማቡካት፣
 • የፉርኖ ዱቄት በተነሰነሰበት ጠረጴዛ ላይ ሊጡን ለአሥር ደቂቃ ያህል ማቆየት፣
 • ቀጥሎም በድቡልቡል እንጨት እየዳመጥን ስስ በማድረግ የምንሠራበትን ድስት መጠን እየለካን መቁረጥ፣
 • በንፁህ ጨርቅ በተሸፈነ ወንበር ላይ ለሃያ ደቂቃ ያህል መዘርጋት፣
 • ቅባት በተቀባ መጋገሪያ ላይ ከሊጡ ወስደን ከሥር ማንጠፍ፣
 • ቀጥሎም ባሽመል፣ ፎርማጆና ስጎ መጨመር፣
 • እንደገና ላዛኛ፣ ስጎ፣ ባሽመልና ፎርማጆ እየጨመርን ያዘጋጀናቸውን በሙሉ እስኪያልቁ ድረስ መደርደር፣
 • በመጨረሻም ማብሰያ ምድጃ ውስጥ ከሃያ እስከ ሠላሳ ደቂቃ ካበሰሉ በኋላ በአራት ማእዘን ቆራርጦ በትኩሱ ማቅረብ።
  • ሰዋስው ‹‹ባህላዊ ምግብ አዘገጃጀት››