የጠጅ አጣጣል

መጠን 

 • 1  ጆግ  ቢጫ  ማር 
 • 2  ጆግ ጌሾ ( በደንብ  የተለቀመ)
 • 3  ጆግ  ውኃ
 • 1/2 ማንኪያ ዕርድ ( ለመልክ ካስፈለገ)
 • 1/2 ጆግ  ጠጅ ( ለእርሾ)

አዘገጃጀት

 1. ውኃውን ለብ ማድረግ
 2. ማሩን ለብ ባለው ውኃ ባግባቡ መበጥበጥ
 3. ጌሾውን በደንብ  አጥቦ የተበጠበጠው ማር ውስጥ መጨመር 
 4. ለእርሾ ያዘጋጀነው ጠጅና ለመልክ ያዘጋጀነውን ዕርድ ጨምሮ በሚገባ ማማሰልና ማዋሃድ እናም ሙቀት ያለው ቦታ በደንብ ከድኖ ማስቀመጥ
 5. እስኪነሳ  ድረስ በየሦስት ቀኑ በእንጨት ማማሰል 
 6. በ12ኛው  ቀን በማጣሪያ ካጣራን በኋላ ያጣራነውን በዕቃ ማስቀመጥ
 7. ከ5 ቀን በኋላ ከላይ የጠለለውን ጠጅ በጠርሙስ ውስጥ መቅዳትና ከስር የሚዘቅጠውን አተላ መድፋት

 

 • ሰዋስው ‹‹ባህላዊ ምግብ አዘገጃጀት››