የጥጃ ስጋና ፎሶልያ

ጥሬ ዕቃ

 • 115 ግራም ቀይ የጥጃ ስጋ
 • 115 ግራም ካሮት
 • 75 ግራም ፎሶልያ
 • 115 ግራም ድንች
 • 350 ሚሊ ሊትር ውኃ

አሠራር

 • ቀዩን ስጋ በትናንሹ መክተፍ፣
 • ድንችና ካሮቱን ልጦ መክተፍ፣
 • ፎሶልያውን መቀንጠስ፣
 • ሥጋውን፣ ድንቹን፣ ካሮቱንና ውኃውን በድስት ውስጥ ከቶ ለ30 ደቂቃ ማንተክተክ፣
 • ፎሶልያውን ጨምሮ ከድኖ አትክልቶቹ እስኪበስሉ ድረስ ለተጨማሪ 10 ደቂቃ ማብሰል፣
 • የበሰለውን ድብልቅ ፈጭቶ መመገብ፡፡

ሜላት ዮሴፍና ህሊና በለጠ፣ (2008)