አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ግራጫ ሾለቅ

‹‹አዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት›› ሾለቅን አፈ ሹል አሞራ ይለዋል፡፡ እሱ ሲጮህ ዝናም ይመጣል ይባላል፡፡ ዶ/ር ከበደ ታደሰ ‹‹የኢትዮጵያ መካከለኛው ስምጥ ሸለቆ ወፎች የኪስ መጽሐፍ›› ላይ ግራጫ ሾለቅ ከሳይንሳዊ ስሙ ጋር አያይዘው እንደገለጹት፣ ‹‹Hemprich’s Hornbill Tockus hemprichii›› ጠቆር ያለ ግራጫ መልክ አለው፡፡ መጠነኛ ሾለቆች መንቆራቸው ደብዛዛ ቀይ ቀለም ያለውና ቀጠን ያለ ረጅም ነው፡፡ የክንፋቸው ሽፋን ላባ ዳር ዳሩ ነጣ ያለ ሲሆን፣ ጅራታቸው ደግሞ ነጭና ጥቁር ቀለም ይፈራረቅበታል፡፡ በድንጋያማና በገደል አካባቢ ይገኛሉ ይላሉ፡፡