አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ፊፋ የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ አገሮችን ቁጥር ወደ 48 አሳደገ

 

የዓለምን እግር ኳስ በበላይነት የሚመራው ፊፋ እ.ኤ.አ. በ2026 ለሚያከናውነው የዓለም ዋንጫ የተሳታፊ አገሮችን ቁጥር ወደ 48 ማሳደጉን ይፋ አደረገ፡፡

ቢቢሲ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ጆቫኒ ኢንፋንቲኖ ጠቅሶ እንደ ዘገበው፣ ማክሰኞ ጥር 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ተቋሙ በዙሪክ ባደረገው ስብሰባ ቁጥሩን ከ32 ወደ 48 ከፍ እንዲል በድምፅ መወሰኑን አስታውቋል፡፡