ፍልፈል

ፍልፈል  አጥቢ እንስሳ ስትሆን፣ በአፍሪካ፣ በአውሮፓ፣ በእስያ እንዲሁም በካሪቢያን ትገኛለች፡፡ 34 ዓይነት ዝርያዎች ሲኖሩ፣ ጅራታቸውን ሳይጨምር ከ24 እስከ 58 ሴንቲ ሜትር ርዝመት አላቸው፡፡ አጫጭር እግሮች ሲኖራቸው፣ ጥፍሮቻቸውን መሬት ለመቆፈር ይጠቀሙባቸዋል፡፡ ረዥም ጭራም አላቸው፡፡

አይጥ፣ ወፍ፣ እንሽላሊትና ነፍሳት የሚመገቡ ሲሆን፣ ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል መጥፎ ጠረን ያወጣሉ፡፡

ያልተጠቀጠቁ ደኖችና ሳር የበዛባቸው ሜዳዎች ላይ የሚኖሩት ፍልፈሎች፣ ክብደታቸው እስከ አራት ኪሎ ግራም ይደርሳል፡፡ በሰዓት 32 ኪሎ ሜትር ያህል ይጓዛሉ፡፡ በአብዛኛው ቡናማና ግራጫ ቀለም ያላቸው ሲሆን፣ የመኖር ዕድሜያቸው ከ10 እስከ 15 ዓመት ነው፡፡