አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ፍሬ ከናፍር

‹‹በሰብአዊ መብቶችና በሰዎች ክብር ላይ የተመሠረቱትን፣ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጣቸውን የግብረገብ (ሞራል) እሴቶች ይጠብቁ ዘንድ ኃላፊነት አለብዎት፡፡››

የሞስኮና የመላዋ ሩስያ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ (ኪርል)፣ ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸው ይፋ ከተደረገ በኋላ የእንኳን ደስ አለዎ መልእክታቸውን ሲያስተላልፉላቸው ካሠፈሩት ኃይለቃል የተወሰደ፡፡

ፓትርያርኩ፣ ተመራጩ ዶናልድ ትራምፕ በእግዚአብሔር ተራዳኢነት ከፍተኛና ኃላፊነት ያለበትን ፕሬዚዳንታዊ መንበር በአስተዋይ ኅሊና፣ በትሁት ሰብእና  መምራት እንዲችሉም ተመኝተውላቸዋል፡፡