አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ፍሬ ከናፍር

‹‹ፕሬዚዳንት ፊደል ካስትሮ ኢትዮጵያዊያን የአገራቸውን ሉዓላዊነት ለመከላከል ባደረጉት ተጋድሎ ያለማወላወል ከጎናቸው የተሠለፉ ታላቅ ወዳጅ ሲሆኑ፣ ይህንንም ታሪክ ምንጊዜም ሲያስታውሰው ይኖራል፡፡››

ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ሰሞኑን ከዚህ ዓለም በ90 ዓመታቸው በሞት ለተለዩት የኩባ ቀድሞ ፕሬዚዳንት ፊደል ካስትሮ የተሰማቸውን ሐዘን ከገለጹበት መግለጫ የተወሰደ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ለኩባ ሕዝብና መንግሥት ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ ፊደል ካስትሮ የኢትዮጵያ ታላቅ ወዳጅ ነበሩ ብለዋል፡፡ በእሳቸው አመራር ወቅትም አያሌ ኢትዮጵያውያን በኩባ በተለያዩ የትምህርት መስኮች እውቀት እንዲገበዩና አገራቸውን እንዲያገለግሉ ያበረከቱት አስተዋጽኦ፣ ለኢትዮጵያ ለነበራቸው አክብሮትና ድጋፍ ህያው ምስክር እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡ የሁለቱ አገሮች ጥብቅ ትስስር በታሪክ ልዩ ሥፍራ የሚሰጠው እንደሆነ በመልዕክታቸው ገልጸው ለኩባ መንግሥትና ሕዝብ፣ እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡