አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ፍሬ ከናፍር

‹‹ቀነኒሳ በቀለ በሪዮ ኦሊምፒክ በማራቶን አለመወዳደሩ ታላቅ ስህተት ነው!››

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ የዓለም ኮከብ አትሌቶች ምርጫ በተካሄደባት ሞናኮ ከተማ ለኤኤፍፒ የዜና ምንጭ የተናገረው፡፡ ጫማውን የሰቀለው ገናናው ሯጭ ኃይሌ ኅዳር 22 ቀን 2009 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ በቅርቡ በተካሄደው የበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ለመስበር ስድስት ሰከንድ አምልጦት ያሸነፈው ቀነኒሳ በቀለ፣ ዘንድሮ ክብረ ወሰኑን እንደሚሰብር እምነቱ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ የኦሊምፒክ 5,000 ሜትርና 10,000 ሜትር ሻምፒዮኑ ቀነኒሳ በቀለ በዘንድሮ የበርሊን ማራቶን ያስመዘገበው 2 ሰዓት 03 ደቂቃ 03 ሰከንድ  ሃቻምና ዴኒስ ከሚቶ በጀርመን መዲና ካስመዘገበው 2፡02፡57 የተቃረበ ነበር፡፡ ‹‹ምንም ይሁን ምንም ለንደን (የዓለም ሻምፒዮና የሚካሄድባት) እየመጣች ነው›› ያለው ኃይሌ፣ ‹‹ታያላችሁ ወይ ዱባይ አሊያም በሌሎች ማራቶኖች ዕድል ከቀነኒሳ ጋር እንደምትቆም›› በማለትም ተናግሯል፡፡