አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ፍሬ ከናፍር

‹‹ግልገል ጊቤ ፫ (3) የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የኃይል እጥረት በመቅረፍ ረገድ የቁርጥ ቀን ደራሽነቱን አረጋግጧል፡፡››

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በ1.5 ቢሊዮን ዩሮ የተገነባውና  1870 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ግልገል ጊቤ ፫ (3) የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ታኅሣሥ 9 ቀን 2009 ዓ.ም. ሲመርቁ የተናገሩት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም ግድቡ የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ  ለሌሎች አገሮች በመሸጥም ከአገሮቹ ጋር ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር የበለጠ እንደሚያሳድገውም አውስተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ፕሮጀክቱ ገጥሞት የነበረውን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ትችት ፣ የመልክዓ ምድርና የፋይናንስ  ችግሮች በጽናት አልፎ ለምርቃት መብቃቱ ለኢትዮጵያ ታላቅ ስኬት መሆኑንም ሳይናገሩ አላለፉም፡፡