አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ፍሬ ከናፍር

‹‹ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ድንገት ተፈጥሮ በ10ሺሕና በ5ሺሕ ሜትሮች ፋና ወጊ ድል በማስመዝገብ፣ የአገራችን ሰንደቅ ዓላማ ደግሞ ደጋግሞ እንዲውለበለብና ብሔራዊ መዝሙራችን እንዲዘመር ያደረገ፣ እንደስሙ ሁሉ የምንጊዜም ምርጥና የቁርጥ ቀን ጀግና አትሌታችን ነው፡፡››

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በ‹‹ማርሽ ቀያሪው›› ገድለኛ አትሌት ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ሥርዓተ ቀብር ላይ ታኅሣሥ 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ፡፡ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተገኝተው የጠቅላይ ሚኒስትሩን የሐዘን መግለጫ መልዕክት ተወክለው ያነበቡት የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትሩ ርስቱ ይርዳው ናቸው፡፡