ፍሬ ከናፍር

‹‹እናንተን ለማገልገል በመቻሌ ክብር ይሰማኛል፡፡ የተሻልሁ መሪ እንድሆን፣ መልካም ሰብእና እንዲኖረኝ አድርጋችሁኛል፡፡››

ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በትዊተር ገጻቸው ያስተላለፉት የስንብት መልዕክት፡፡ አሜሪካን ለስምንት ዓመታት የመሩት 44ኛው ፕሬዚዳንት የነበሩት ባራክ ኦባማ፣ ሥልጣናቸውን ቢለቁም ኅብረተሰቡ ባሰነቃቸው የእውነትና የፍትሕ፣ የለዛና የፍቅር ድምፆች አማካይነት የዜግነት ተግባራቸውን እንደሚቀጥሉ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡