ፍሬ ከናፍር

‹‹በአፍሪካ ውድቀት ካሳየን በመላው ዓለም መውደቃችን አይቀሬ ነው!››

አዲሱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ፣ በ28ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ላይ ለመገኘት አዲስ አበባ በመጡበት ወቅት የተመድ ኤጀንሲዎች ሠራተኞችን እሑድ፣ ጥር 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ባነጋገሩበት ወቅት፣ በአፍሪካ የሚደረጉ የተመድ የሰላም፣ የፀጥታና የልማት እንቅስቃሴዎች ስኬታማነት በዓለም መድረክም ውጤታማነቱን የሚያረጋግጡ በመሆናቸው የተመድ ሠራተኞች በሙሉ ፖሊሲዎችን በውጤታማነት እንዲያፈጽሙ ተናግረዋል፡፡