አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ፓስታ በአትክልት

- ግብአቶች

3 ቲማቲሞች 

175 ግራም ዝኩኒ

75 ግራም ነጭ እንጉዳይ (መሽሩም)

115 ግራም የፈረንጅ ቃርያ

20 ሚሊ ሊትር (4 የሻይ ማንኪያ) የቲማቲም ድልህ

250 ሚሊ ሌትር ውኃ

40 ግራም ፓስታ

  •  
  1. ቲማቲሞቹን በሰያፍ ቆርጦ ጎድጓዳ ሣህን ውስጥ መክተት፣ የፈላ ውኃ መሙላት፡፡ ለአንድ ደቂቃ አቆይቶ አጥልሎ መላጥ፣ አራት ቦታ ከፍሎ ፍሬዎቹን ማውጣት፡፡
  2. ዝኩኒውንና እንጉዳዩን መቀንጠስ፣ የቃሪያውን ፍሬ ማውጣት፡፡
  3. አለቅልቆ እንጉዳዩንና ዝኩኒውን በስሱ መቆራረጥ፡፡ ቃሪውን መክተፍ፡፡
  4. ድስት ውስጥ መክተት፡፡ የቲማቲም ድልሁንና ውኃ ጨምሮ ለ10 ደቂቃ ከድኖ ማንተክተክ፡፡
  5. አትክልቱን ማንተክተክ፣ ፓስታውን የፈላ ውኃ ውስጥ መክተትና እስኪበስል ድረስ ከ10-15 ደቂቃ መቀቀል፡፡ ሲበስል ማጥለል፡፡
  6. አትክልቱንና ፓስታውን ደባልቆ በመፍጫ ማሽን መፍጨት፡፡
  7. ጥቂት በጎድጓዳ ሣህን ላይ በማንኪያ አውጥቶ መመገብ
  8. ለማቀዝቀዝ የሚመች ምግብ ነው፡፡
  9. ፡ ልጅዎት ደፋር ተመጋቢ ከሆነ አንዷን የነጭ ሽንኩርት ፍልቃቂ ለሁለት ሰንጥቀው ግማሹን ፈጭተው በቁጥር 3 ላይ ጨምረው ምግቡን ማዘጋጀት ይቻላል፡፡

* * *

ሜላት ዮሴፍና ህሊና በለጠ፤ ጣዕም ያላቸው የሕፃናት ምግቦች (2009)