‹‹አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ለኔ የሙያ አባቴ ናቸው፡፡››

 

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት ኢሳ ሐያቱ፣ ለ39 የካፍ ጉባኤ አዲስ አበባ በደረሱበት መጋቢት 4 ቀን 2009 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ የተናገሩት፡፡ ካሜሩናዊው የካፍ ፕሬዚዳንት ከ29 ዓመታት በፊት መንበሩን የተረከቡት ነሐሴ 13 ቀን 1979 ዓ.ም. ካረፉት ኢትዮጵያዊው አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ነበር፡፡ አቶ ይድነቃቸው ካፍን ከ60 ዓመታት በፊት ከመሠረቱት አንዱና በቅድሚያ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ከ1964 ዓ.ም. ጀምሮ ዳግም እስካረፉበት ድረስ ለ15 ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡