• ከሩብ ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኞች አሉት

የኦሮሚያ ልማት ማኅበር (ኦልማ) በክልሉ ለሚያከናውናቸው የተለያዩ የልማት ሥራዎች በሥነ ምግባር ግንባታ፣ በክህሎትና በዕውቀት የካበተ ቀጣይ ትውልድ ለማፍራት በጎ ፈቃደኝነት ላይ ትኩረት መስጠቱን አስታወቀ፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥርዓት ማኑዋልም ይፋ አደረገ፡፡

በአንዴ ከስድስት ሰው በላይ መያዝ በማይችለው የእንፋሎት (ስቲም) መታጠቢያ ክፍል ውስጥ በከፊል የተሸፈኑ ሴቶች ተደርድረዋል፡፡ ከሁለቱ በስተቀር የተቀሩት እርስ በርስ አይተዋወቁም፡፡ 

በኢትዮጵያ የተሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ከተቀበሉት 285,628 ተፈታኞች መካከል 42 ከመቶ 350 ነጥብና ከዛም በላይ ማምጣታቸውን የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞችን ያሳተፈ ሁለንተናዊ ልማት ለማካሄድ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽኖችን ፈርማለች፡፡ በአገር ውስጥም አካል ጉዳተኛውን ያካተተ ኢኮኖሚያዊ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት እንዲኖር አዋጅና ፖሊሲ ወጥቷል፤ መመርያም ተዘጋጅቷል፡፡

‹‹መቼም ገንዘቡ ካለቀ እኛም አለቅን ማለት ነው፤›› አሉ የሆስፒታሉ አልጋ ላይ ጋደም እንዳሉ፡፡ በግምት በ60ዎቹ መጀመርያ ላይ የሚገኙት እኚህ ሰው ኩላሊታቸው ሥራውን ካቆመ ዓመታት አስቆጥሯል፡፡ 

የለበሱት በዝናብ ርሧል፡፡ ችግኝ ለመትከል በተመረጠው በእንጦጦ ማርያም ጋራ ላይ የተገኙት ማልደው ነው፡፡ በግምት ሁለት መቶ የሚሆኑ በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የሚሠሩ ሰዎች ናቸው፡፡ 

Pages