መነሻው በደቡብ አሜሪካ ከፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ የሆነውና በአካባቢው በሚፈጠር የውኃ ሙቀት መጨመር የሚከሰተው ኤልኒኖ ከሁለት እስከ ሰባት ዓመታት እየቆጠረ ይመጣል፡፡  

የጤና ተቋማትን፣ የጤና ባለሙያዎችን፣ መድኃኒቶችን፣ ምግብና ምግብ ነክ ነገሮች ላይ ፍተሻና ቁጥጥር ለማድረግ በአዋጅ ቁጥር 661/2002 የተቋቋመው የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለሥልጣን ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ላይ የ2009 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቧል፡፡

አርሶ አደሩ አቶ ዳዲ ጅራ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ከአዳማ ከተማ አቅራቢያ (ወንጂ ማዞርያ) በ65 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነቡት ሆቴል አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ 231 ከተሞች ጎንደር ሰንብተዋል፡፡ ሰባተኛውን የከተሞች ፎረም ሚያዝያ 22 ቀን 2009 ዓ.ም.  በይፋ የተከፈተው በፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ሲሆን፣ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ዘልቋል፡፡ 

በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚታዩትን የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ 300 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና አሥር ዩኒቨርሲቲዎች በክላውድ ቴክኖሎጂ መረብ ለማስተሳሰር ዝግጅት ላይ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

Pages