​ከስድስት ዓመት በፊት የወጣው የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ደንብ በአሽከርካሪዎችና በእግረኞች ላይ የጣለው ቅጣት ደካማና እጅግ የላላ መሆኑና በዚህም የተነሳ በቁጥጥሩና ክትትሉ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

​ጠመዝማዛውን መንገድ ጨርሰው  የዳዬ ከተማ መግቢያ ላይ ብቅ ሲሉ በርካታ የሞተር ሳይክሎች ይመለከታሉ፡፡ አልፎ አልፎም ባለ ሦስት እግር ባጃጆች ይታያሉ፡፡ ሞተር ሳይክሎቹ ግን ለከተማው ነዋሪዎች ብቸኛ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡

​ለሁለንተናዊ ዕድገት አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ተብለው በመተግበር ላይ ከሚገኙት 17 ዘላቂ ልማት ግቦች መካከል 12ቱ የሚሳኩት የሥርዓተ ምግብ ችግሮች ሲፈቱ ብቻ መሆኑን በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የእናቶችና ሕፃናት ጤና ዳይሬክቶሬት፣

በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን፣ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ አገር  በቀል የሆነው የሞሪንጋ ተክልን የምርት እሴት በመጨመር የአካባቢውን ኅብረተሰብ የሥነምግብ ሁኔታ ለማሻሻል፣ እንዲሁም የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማጎልበት የሚያስችል የአምስት ዓመት ፕሮጀክት የካቲት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በይፋ ተበሰረ፡፡

Pages