በአፍሪካ ከ70 ዓመታት በፊት ወዲህ ታጥቶ የማይታወቀውን ድርቅና ረሃብ ለመታደግ የዕርዳታ ሰጪዎች ዕርጥባን ወሳኝ ቢሆንም፣ ሰብአዊ አገልግሎት ላይ ለሚሠሩ ድርጅቶች የሚደረግን የበጀት ድጎማ መቀነስ ሊነገር የማይችል ቀውስ እንደሚመጣ በአፍሪካ የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል፡፡ 

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) በየመንና በጂቡቲ በችግር ላይ የነበሩ 146 ኢትዮጵያውያን ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ 

የሴቶች አጀንዳ በለውጥና ትራንስፎርሜሽን ፓኬጅ ውስጥ ተካቶ በተግባር የሚታዩ ለውጦች ቢመዘገቡም፣ የሴቶች ጥቃት አሁንም አሳሳቢ መሆኑን የኢትዮጵያ የሴቶች ማኅበራት ቅንጅት (ኢሴማቅ)ዳይሬክተር አስታወቁ፡፡

በሁለተኛው የዕደገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከ12 ሚሊዮን ሔክታር በላይ የሚሆን ቦታን በመኸር ሰብል ለመሸፈን መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በ8ኛው አገር አቀፍ የአርሶ/አርብቶ አደሮች በዓል በአዳማ በተከበረበት ዕለት ገልጸዋል፡፡

Pages