የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከመድኃኒት ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ስህተቶችን በአምስት ዓመት ውስጥ በግማሽ መቀነስ የሚያስችለውን ዕቅድ ማውጣቱን ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ አስታወቀ፡፡

የአሜሪካ መንግሥት የበሽታዎች ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ) ከአሜሪካ ፕሬዚዳንት የአስቸኳይ ዕቅድ ለኤድስ ድጋፍ (PEPFAR) ባገኘው 150 ሚሊዮን ብር ያስገነባው ዘመናዊ ብሔራዊ የኅብረተሰብ ጤና ማሠልጠኛ ማዕከል፣ መጋቢት 19 ቀን 2009 ዓ.ም. ተመርቆ ለኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ተቋም በይፋ ተላለፈ፡፡

ፖሊሲ አውጪዎች ስለ አርብቶአደሩ ያላቸው ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆን፣ ለዘርፉ አዋጭ ፖሊሲና የልማት ድጋፍ እንዳይኖር ማድረጉን ‹‹የአርብቶ አደርነት የወደፊት ዕጣ ፈንታ በኢትዮጵያና የፖሊሲ አማራጮች›› በሚል ማኅበራዊ ጥናት መድረክ ያስጠናው ጥናት አመልክቷል፡፡

በአፍሪካ ከ70 ዓመታት በፊት ወዲህ ታጥቶ የማይታወቀውን ድርቅና ረሃብ ለመታደግ የዕርዳታ ሰጪዎች ዕርጥባን ወሳኝ ቢሆንም፣ ሰብአዊ አገልግሎት ላይ ለሚሠሩ ድርጅቶች የሚደረግን የበጀት ድጎማ መቀነስ ሊነገር የማይችል ቀውስ እንደሚመጣ በአፍሪካ የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል፡፡ 

Pages