​እንደወትሯቸው ማልደው ተነስተው ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም ተያይዘው ወጥተዋል፡፡ ልጆቻቸውም እነሱን ተከትለው በየፊናቸው ተሰማርተዋል፡፡  ዕለቱን በዚህ መልኩ በተለመደው ሁኔታ የጀመሩት ቢሆንም ፍጻሜው ግን ልብ የሚሰብር ነበር፡፡ 

​በታዳጊ ክልሎች የሦስተኛ ወገን መድን አዋጅን ተከትሎ የወጣው የተሽከርካሪ  አደጋ ተጎጂ የአስቸኳይ ሕክምና አገልግሎት አፈጻጸም መመሪያን በመተግበር ረገድ ክፍተቶች መታየታቸውን የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

​መጠጣትና ማጨስን ከአሥር ዓመታት በፊት ስትጀምረው ለመዝናናት በማሰብ እንጂ ከማትወጣበት የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የጤና ቀውስ ይከተኛል ብላ አልነበረም፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለች ከጓደኞቿ ጋር የጀመረችው መጠጥና ሲጋራ ግን ከአሥር ዓመት ላላነሰ ጊዜ አብሯት ዘልቋል፡፡ 

​ኢትዮጵያ በተለያዩ አራት የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎች ፓርኮች ላይ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ለማከናወን እንዲያስችላት ለቀረጸችው የሰባት ዓመት ፕሮጀክት 7.3 ሚሊዮን ዶላር በዓለም ባንክ ቡድን መጽደቁን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳትና ልማት ባለሥልጣን (ኢዱልጥባ) አስታወቀ፡፡ 

Pages